EWNET ABSARI EVANGELICAL CHURCH

እውነት አብሳሪ

ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን
ወደ ቆላስይስ 1 28 ፤
እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው።

ክረስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ መለኩታዊ ሥርዓትን በማራመድ ሁለንተናዊ አገልግሎት ለመስጠት  የታጠቀ ትውልድ  ማነሳሳት፡፡

1.2.1 የደህነት ወንጌል ከመስበክና ከማስተማር ባሻገር አማኞች የደቀመዝሙርት ሕይወት እንዲኖሩና የክርስቲን ባለአደራነትን እንዲረዱ በማድረግ በሥራ እንዲተረጎሙ ማደፋፈርና ፍሬያማ ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት፡፡ 
1.2.2 ደቀ መዝሙር አድራጊዎች በማስልጠን ከታዳጊ ክርስቲያኖች ጋር መለኮታዊ ስርዓትንና አባታዊ ግንኙነትን በመፍጠር ለበለጠ ኃላፊነት ማዘጋጀት፡፡
1.2.3 እማኞች በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ክርስቶስን ማዕከላዊ ያደረገ አካሄድ እንዲኖራቸው በቃልና በስራ ብርቱ የሆነ ምሳሌነት መስጠት፡፡
1.2.4  የሰው ፍላጎት መንፈሳዊ እንደመሆኑ ሥጋዊም ስለሆነ በሕፃናት፣በወጣቶች፣በአረጋውያን፣መበለትና እና ሌሎች ዙሪያ ምግባር ሰናይ አገልግሎት መስጠት፡፡ 

3.1 መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይና አዲስ ኪዳን) በምልዓት በእግዚአብሔር  መንፈስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ታምናለች፡፡ እንዲሁም ሊታመንበት የሚገባው በሰው እምነትና ሕይወት ላይ የመጨረሻ ስልጣን ያለው  የቤተ ክርስቲያን  እምነት ሥርዓት  መሰረት እርሱ ብቻ መሆኑነ  ታምናለች፡፡ (1ቆሮ.1፡22፡2ጢሞ.3፡16፣ሮሜ15፣14፣ ዩሐ3፣6፣1ቆሮ.10፣11)

3.2 እግዚአብሔር አብ
እግዚአብሄር በፍቅሩ ከእስራኤል ሕዝብ ጋ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት  የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ በለጁ በእየሱስ ክርስቶስ ኅንነት አንዳዘጋጀ እርሱን ተቀብለው ኃጢአታቸውን ለሚናዘዙ ሁሉ የእግዚአብሔር  ልጆች ይሆኑ ዘንድ  ስልጣን እንደሰጣቸው ታማናለች፡፡ (ዘፍ.17፣1፣ ዘዴ3፣15፣6፣2-5፣ኢሳ.63፣16፣1ቆሮ.8፤6፣ኤፌ.4፡6)

3.2.2 እግዚአብሔር ወልድ

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ልጅ መሆኑን፣ በመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ ኃጢአት  ያልሰራ መሆኑን፣ሰውን ለመዋጀት ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ራሱን ቤዛ  አድርጎ በመስቀል ላይ መሞቱን፣ በሦስተኛው ቀን ከሞት መነሳቱን፡ በክብር ማረጉን ለእኛም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት መኖሩን፡፡ የቤ ክርስቲናቸውን መስራችና  ራስ መሆኑን፣ ደግሞም  ለፍርድ እንደሚመጣ ታምናለች፡፡ (ዘፍ.3፡13፣ኢሳ.53፣1ጢሞ.3፡ 16፡ዕብ1፡8፡4፣ 5፡7፡25፡9፡ 12፡13፡8፡1 ጴጥ.2፡22)

3.2.3 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ምልዓተ አካል እንዳለውና  መለኮት መሆኑን፣ዓለምን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅ ፣ ስለ ፍርድ እንደሚወቅስ፣በምዕመናን ውስጥ አድሮ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው፣ እንደሚያጽናናቸው የቅድስና ኑሮ ለመኖር እንደሚያስችላቸው፣ ለአገልግሎትም ኃይልንና የፀጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጣቸው ታምናለች፡፡ ዛሬም ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚጠመቁና በልዩ ቋንቋ (ልሳን) እንደሚናገሩ ታምናለች (ዘፍ.1፡2፣ዩሐ7፡37-39፣ሐዋ.2፣3-4፣8፣14-17፣10፣45-46፣19፣6-7፤ 1ቆሮ.12፡10፡14፡4-5)

3.3 ደኀንነት (አዲስ ፍጥረት)
ሰው በመጀመሪያ ያለ ኃጢአት መፈጠሩን ታምናለች፡፡ ይሁን እንጂ ሰው በፍቃደኝነት ኃጢአት ላይ በመውደቁ ምክንያት  የኃጢአት  ባሕርይ ይዞ መወወለዱን እንዲሁም በኃጢአቱ ተጸድቶና ንስሃ ግብቶ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው  የመስቀሉ ሥራ በማመን በፀጋ ብቻ እንደሚድንና  እንደሚጸድቅ ዳግመኛ በመንፈስ ቅዱስ  በመወለዱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚሆን፣ በክርስቶስ  መንፈሳዊ በረከትና የዘላለም ሕይወትን እንደሚያገኝ ታምናለች፡፡ (ዩሐ12፡13፡3፡48፡16፡ሐዋ.13፡38-39፡ ሮሜ 3፡20-26፡10፡9-10፡ አፌ 2፡8-9)

3.4 መለየትና ቅድስና
ምዕመናን ከዓለማዊነትና በዓለም ከሚገኙ ከንቱ ነገሮች ተለይተው ለእግዚአብሔር ክብር በኢየሱስ ክርስቶስ ፍርድ እንደሚወቅስ፡ በምዕመናን ውስጥ  አድሮ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው፡ እንደሚየጸናናቸው፡የቅድስና ኑሮ ለመኖር እንደሚያስችላቸው፡ ለአገልግሎትም፡ ኃይልንና የፀጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጣቸው  ታምናለች፡፡ ዛሬም ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚጠመቁና በልዩ ቋንቋ(ልሳን) እንደሚናገሩ ታምናለች፡፡

ምዕመናን ከዓለማዊነትና በዓለም ከሚገኙ ከንቱ ነገሮች ተለይተው ለእግዚአብሔር  ክብር በኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅኑሮ መኖር እንደሚገባ ታምናለች፡፡ (ዩ.17፡15፡2ቆሮ.6፡14፡18፤ ሮሜ 12፡1-2፡1ጴጥ.2፡9፡1ዩሐ.2፡9፡2፡15-16፡ዕብ 12፡14፤1ተሰ.4፡13-18፤1ዩሐ.2፡28)

3.6 ቅዱሳን መላዕክት
ቅዱሳን መላዕክት ሕያዋን መሆናቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንዳሉ፣ቅዱሳንን እንደሚያገለግሉና ጌታ ሲመጣ አብረው እንደሚገለጡ ታምናለች፡፡ (1ነገ.19፤5-7፤ማቴ.1፡20-22፡2፡13፡28፡28፡ሉቃ.1፡11፡20፡16፡22፡1ተሲ4፡16፡ራዕይ 1፡14፡14፡10)

3.7 ሰይጣን
ሰይጣን እርኩስ መንፈስ መሆኑን፤ የጥፋት ሁሉ ምንጭ በእግዚአብሔር መንግስትና ዕቅድ  ላይ ያመጸሐሰተኛ አባት መሆኑን፡ በመጨረሻም ከተከታዮች ጋር ወደ ተዘጋጀለት ወደ ገሃነመ እሳት እንደሚመጣል ታምናለች፡፡ (ዘፍ.3፡1-5፡ኢሳ.14፡12-15፡ዩሐ.8፡44፡2ቆሮ.11፡14፡1ጴጥ.5፡8
ራዕይ 2፡10)

3.8 ፍርድ
ኢየሱስ ክርስቶስ  በመጨረሻም በክብር  በመኒገለጥበት ጊዜ በክርስቶስ አዳኝነት  ያመኑ (ጻድቃን) ከእርሱ ጋር ለዘላለም በመንግስተ ሰማይ እንዲያርፉ ሲፈረድላቸው በክረስቶስ አዳኝነት ያላመኑ (ኃጥአን) በገሃነም ለዘላለም እሳት ውስጥ እንዲጣሉ እንደሚፈረድባቸው ታምናለች፡፡ ሰይጣንና መላዕክቱም በእሳት ባሕር  ውስ እንደሚጣሉ ታምናለች፡፡ (ማቴ.25፡31-46፡ሉቃ.13፡23፡30፡16፡19-30፤ራዕይ 7፡9-17፤20፡10-15)

3.9.1 የውኃ ጥምቀት
የውኃ ጥምቀት መከናወን ያለበት ሰዎች ስለ ኃጢአታቸው  ንስሃ  ገብተው ከክርስቶሰ ጋር  መነሳታቸውን ለዓለም የሚያረጋግጡበት፡የሚመሰክሩበትም መሆኑን ታምናለች፡፡ የጥምቀት ሥርዓት በአብ፡በወልድ፡በመንፈስ ቅዱስ።

ቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መገለጫዎችን መሰረት አድርጋ የተቋቋመችው ለሚከተሉት ዓላማዎች ነው፡፡
4.1 የእግዚአብሔርን ቃል በሙላት መስበከና ማስተማር፡፡ (ማቴ.4፡23፣ኤፌ 4፡12-13፡5፡2፡2ጢሞ.4፡1-2
4.2 ሰዎች ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት እንዲያውቁና አምነው እንዲድኑ በዚህ በኩል የሚገኘውን ዘላለማዊ ሕይወት በምልዓት እንዲያገኙ ማበረታታት፡፡ (ማቴ.9፡35፡2ጢሞ.4፡1-2፡1ዩሐ.5፣11-12)
4.3 የክርስቲያኖች እምነትና ታማኝነት እንዲጠናከር ለጸሎት፣ለምክርና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት እማኞችን ማደራጀት፡፡ (ማቴ.9፣35፣ሐዋ.1፡14፡2፡1-1፡1ዩሐ.5፡11-2)
4.4 ቤተክርስቲያኗ በሐዋርያት፡ በነቢያት፡ በመጋቢ፡በአስተማሪና በወንጌላውያን አገልግሎት ስለምታምን ስለዚህ አገልግሎት የተጠሩ ሰዎች አገልግታቸውን በሙላት እንዲሰጡ ማበረታታት፡፡ (ሕዋ.13፡1-14፡አፌ4፡11፤1ቆሮ.12፡28)
4.5 በአብያተ ክርስቲያናትና በወንጌል አማኞች መካከል አንድነትና ሕብረት እንዲኖር ትረት ታደርጋለች፡፡
4.6 ስለ ሰዎች ሁሉ፡ስለመንግስና ስለ ባለስልጣንናት ሁሉ ልመና፤ጸሎትና ምልጃ  ማድረግ፡፡ (ጢሞ.2፡2)
4.7 በሥነ ምግባር የታነጸ ብቁ ዜጋ ማፍራት፡፡
4.8 የልማት ድርጅት በማቃቃም መንግስትና ሕዝብን የሚጠቅሙ የልማት ሥራዎች መስራት፡፡
4.9 አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ከዚህ በላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የቤተክርስቲያኒቱን ዓላማዎች የማስፈጸም ኃላፊነት ይኖራቸዋል፡፡ 

5.1 ጽሑፍ፣ጀማ ስብከት ፣በራሪ ወረቀት፣ኦዲዮ ቪዲዮ፡ጋዜጣ፤ መጽሄት ማሳተምና  ኤሌትሪክ ሚዲ መጠቀም ፡፡
5.2 የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶች በማቋቋም የአገልግሎት ጥሪ ያላቸውን ለወንጌል ሥራ ማሰልጠን፡፡
5.3 የብዙሃን መገናኛዎችን በመጠቀም ወንጌልን ማሰራጨትና ማስተማር፡፡
5.4 በጸሎት፣በገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ከሚመለከታቸው ጋር በአንድነት መሥራት፡፡
5.5 መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚረዱ የትምህርት መረጃዎችንና ማስተማሪያ መጽሐፍትን እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት መሣሪያዎችን በመናዘጋጀት ማሰራጨት፡፡
ምዕራፍ፡- ቤተክርስቲያንና ፖለቲካ
6.1 ቤተ ክርስቲያኗ ለኃይማኖት  ተግባር ብቻ እንድትውል ተቋቁማለች፡፡ ስለሆነም ትርፍ አልባ ከፖለቲካ ነፃ የሆነች ናት፡፡ ቤተክርስቲያኗ በምንም ዓይነት መንገድ የሀገሪቱን ሕግና የፖለቲካ ይዘት የሚተች ወይም ሊያዛባ የሚችል ጽሑፍ አታሰራጭም፡፡
6.2 ቤተክርስቲያኗ በምንም ዓይነት  ለመመረጥ፣ወይም የፖለቲካ ዘመቻ  ለሚያደርጉ ግለሰቦች ድጋፍ አትሰጥም ፡፡

Sermon
Colossians 1:28
whom we proclaim, admonishing every man and teaching every man in all wisdom, that we may present every man perfect in Christ

To capture generation for Lord Christ by preaching the word of God focusing on Christology and humble service and stewardship.

Practice
1.2.1 Preaching the Gospel of salvation to believers and encourage them to be good steward and desciple in order that their life bring forth fruit.
1.2.3
Pastors will develop pastoral relationship among the belivers to train them as disciplines.
1.2.4 pastor ought to live exemplary life sothat believers will follow them to live christ like life.philanthropic activities for widows and the poor to obey Jesus by outreaching others.

Church believes that Bible (old and new testament) is written by the God spirit and has exclusive power in the life of people and our faith relies only on him.
1 Corinthians 1:22; 2 Timothy 3:16; Roman 15 :14 John 3:6 1 Corinthians 10:11

We believe that God love has revealed through Christ Jesus by Abraham covenant with God and we believe whoever believe in Jesus will have everlasting life and to be the son of God.Genesis 17:1; Deuteronomy 3: 15, 6:2-5, Isaiah 63:16; Ephesians 4:6
3.2.2 God the Son
We believe. Jesus is the Son of God born of virgin Mary .We believe he is man and he is God as well.we believe He died on the cross redeem and reconcile all who believe in him.we believe that he died on the cr
oss and rose from the dead and now on God right hand interceding for us. He is the founder of Church.Genesis 3:13; 1
Timothy 3:16; Hebrew 1:8;5:7 25:9 ; 1peter 2:22

3.2.3 God Holy spirit
The third person in Trinity.He convicts the world for sin.
Basic Christian theology.
From Gospel light international Church education department.
Discipleship
Holy spirit indwelling in believers and cinvicts sin and lead them to truth.Without Him nothing can be done.Miracles,healing,exorcism, righteous living are due to his presence.Even nowadays, people are babtisized with Holy spirit and speak in tongue.Genesis 1:2; John 7:37; Acts 2:3
-4; 8:14; 10:14

We believe man was created sinless before his chooses to sin and death became the legacy of mankind but by believing in Jesus Christ and the work of the Cross all can be righteous and get the right to be children of God.Everlasting life is als obtained by believing in Jesus Christ. John 12:13; 3:48; Acts 13:38; Roman 3:20, 10:9 Ephesians 2:8-9

We believe that Christian should live in holiness and sanctification for God to obey and follow Jesus Christ.John 17:15; 2 Corinthians 6:14; Roman 12:1-2; 1 peter 2:9;
1 John 2:9; 2:15-16; Hebrew 12:14; 1 Thessalonians 4:13-18, 1 John 2:28

We believe that Holy Angeles are eternal and now are serving God and will come with Jesus in his second coming.1 king 19:5 :mathew 1:20-22 ;2:13 ; 28:28 Luke 1:11; 20:16: Revelation 1:14; 14:10

We believe satan evil spirit and the source of all destruction.He is adversary of God kingdom and rebellious and native liar and he will be cast into lake of fire with his fallen Angeles finally.
Genesis 3:15; Isaiah 14:12-14; John 8:44 ; 2 Corinthian 11:14; Revelation 2:10

During judgment day, believers will inherit the king dom of God and non believers wil be cast into lake of fire.The devil and his Angeles will also be cast into fire.Mathew 25 31:46; Luke 13:23-30; 16:19-30; revelation 7:9-17 ; 20:10-15

3.9.1 Baptism
Babtism is performed in the Name God ,Son and Holy Spirit for repentants to symbolize their death for sim and resurrection for righteousness.

4.1. Preaching and teaching of the Word of God is our first priority.
Mathew 4:23; Ephesians 4:12-13 5:2-2; 2Timothy 4:1-2;1 John 5:11-12
4.2 working and praying for all people to know Jesus and believe in him for everlasting life. Mathew 9:35; 2 Timothy 4:1-2 Encourage all people should get salvation and everlasting life by believing Lord Jesus Mathew 9:35 ;2 Timothy 4:1-2; 1john 5:11-12
4.3 strive to strengthen the obedience and faith of fellow Christians for prayer exhortation, word of God etc.mathew 9:35; Acts 1:14; 1 John 5:11
4.4 As the church believes in office of Pastoral, evangelical, prophetic ,desciplship and teaching, it prays that God will grant us and respect their callings.Acts 13:1-14, Ephesian 4:11; 1 Corinthian 12:28

4:5 we strive for unity and oneness among the churches and the congregations.
4.6 we pray for kings and all that are in authorities and all people, and do supplication, intercession.
4.7. Building disciplined and responsible generation.
4.8. Establishing philanthropic and charitable organization, outreaching the needy ones.
4.9. All local churches have responsibilities to do the aforementioned activities.

5.1 To preach the Gospel, church uses printed media,tracts,radios,vedio, magazines even Congregational preaching.
5.2 By founding Bible College, training and equipping those who have calls for gospel.

5.3. Using mass Media, preach the good news of Gospel.
5.4. Working with other fellow believers in preaching, finance and ministries.
5.5 Gathering teaching aids, textbooks, animations that are useful for gospel preaching and make proper use of them.
Church and politics
6.1. Church activities are strictly confined to spiritual activities. Never ever involves in political activities neither to support nor to oppose anyone individual or party whatsoever.
6.2. No political initiative nor any gathering regarding politics is accepted. It is totally against the church’s vision.

 

MISSION
Because of the grace we have received, worshiping God and fellowshiping with one another through the love of Christ, we strive to preach the gospel to our community members.
BIBLE STUDY
Our Church believes, confess and teaches, and upholds the truth of God’s Word, that the Bible is God’s revealed Word to us, spoken in Law and Gospel. The Bible is the source and norm of our ministry, and the final authority for us in all matters of our faith and life.
Active Participation
Building a culture of participation to encourage believers to actively involve in the work of the church.
Christ centered church

Be God's instruments in creating new people who delight in God.